ፍቅረኛሽ የምር እንደሚወድሽ እንዴት ታውቂያለሽ? ወንድ ልጅ የህይወት አጋሩ ሊያደርጋት የሚፈልጋትን ሴት ሲያገኝ እርሷን ለመቅረብ፣ለማስደሰትና ከእርሷ ጋር ጊዜ ለማሳለፍ ማንኛውንም መስዋዕትነት ይከፍላል። የኔ እህት ከታች የተዘረዘሩትን ነገሮች የሚያደርግ ወንድ ካጋጠመሽ ጠበቅ አድርገሽ ያዢው። ከልቡ የሚያፈቅርሽ ወንድ የሚያሳያቸው ምልክቶች 1. #ከአንቺ_ጋር ለመሆን ቆራጥ ነው። ነገሮች ሲመቹ ብቻ ሳይሆን በአስቸጋሪ ጊዜ እንኳን ከአንቺ አይለይም። 2. ከችግሮች አይሸሽም። በግንኙነታችሁ ችግር ሲፈጠር እንዴት በእርጋታና በውይይት መፍታት እንዳለበት ያውቃል። ቂምን ወይም መጥፎ ስሜትን አፍኖ ማስቀመጥ አንድ ቀን እንደሚፈነዳ ያውቃል። ስለዚህ አለመግባባቶች ሲፈጠሩ ወዲያው ለማስተካከል ይጥራል። 3. ለትንንሽ ነገሮች እንኳን አትኩሮት ይሰጣል። አንቺ ትልቅ ቦታ የምትሰጪያቸውን ነገሮች ያውቃል። ለእርሱ ተራ መስሎ ቢታየውም እንኳን ያከብራል። አንቺ የምትወጂያቸው ምግቦች ቤት ውስጥ መኖራቸውን ያረጋግጣል። የምትወጂውን አይነት ፊልም ከአንቺ ጋር ካልሆነ አያይም።አንቺን ለማስደሰት ቤቱን በፅዳት ይይዛል። 4. ብልህና አስተዋይ ነው። ብልህነቱን እንዴት መጠቀም እንዳለበት ያውቃል። ምክር ይሰጥሻል፣ትክክለኛ ውሳኔዎችን ይወስናል። ልትተማመኚበት የምትችይው አይነት ሰው ነው። 5. ለራስሽ ፍቅር እንዲኖርሽ ይፈልጋል። 6. ስላንቺ ችግር እንደራሱ ችግር ይጨነቃል። ያንቺ ሀሳብ የእርሱም ሀሳብ ነው። በችግርሽ ጊዜ ከጎንሽ አይጠፋም። ግን ለራስሽ ጊዜ ስትፈልጊም ያውቃል። ብቸኝነት እንዲሰማሽ አይፈቅድም። በክንዶቹ እቅፍ አድርጎሽ ሁሉን ነገር ለማስተካከል ይጥራል። 7. በራሱም ሆነ ባንቺ ስህተት ስቆ ዝም ይላል። ማንም ሰው ፍፁም እንዳልሆነ ስለሚያውቅ አ...