Skip to main content

Posts

Showing posts with the label ምክሮች

በጧት የሚላኩ የፍቅር መልዕክቶች

  ሁሌ በጥዋት ለፍቅር አጋርህ መልዕክት ብትልክላት የፍቅር ህይወትህን የበለጠ ያጣፍጠዋል፡፡ እንደምትወዳት እና የተለየች ሴት እንደሆነች እንዲሰማት ያደርጋል፡፡ ቀኗን ብሩህ ለማድረግ ከእነዚህ መል ዕክቶች   የወደድከውን Copy Paste አድርገህ ላክላት፡፡        የኔ   ፍቅር እንኳን አዲስ ቀን በህይወትሽ ተጨመረልሽ፡፡ አፈቅርሻለሁ እሺ፡፡ መልካም ቀን ይሁንልሽ፡፡        እየሰመጠ ያለ ሰው አየርን የሚወደውን ያህል እወድሻለሁ፡፡ ደስ የሚል ቀን ይሁንልሽ የኔ ውድ          አንቺ ፊልም ብትሆኚ ብዙ ጊዜ ደጋግሜ አይሽ ነበር፡፡        ትክክለኛዋን ሴት ለማግኘት ብዙ ታግሻለሁ፡፡ በመጨረሻም ትዕግስቴ ፍሬ አፍርቶ አንቺን አግኝቻለሁ፡፡       ባየሁሽ ቁጥር እንደገና ፍቅር ይይዘኛል፡፡ አንቺ ለኔ ልዩ ሴት ነሽ፡፡        የአለማችን ቆንጅዬዋ ሴት እንዴት አደረች?         በጧት ደስ የሚሉ ሀሳቦችን ማሰብ ቀኑን በደስታ ለማሳለፍ ወሳኝ ነው፡፡ ሁል ቀን ደስ ብሎኝ የምውለው አንቺን ስለማስብሽ ነው፡:              ተደሰቺ ስለአንቺ ለሚጨነቅ ሰው መልዕክት ደርሶሻል፡፡        አንቺን ከማሰብ ጋር ፍቅር ይዞኛል       ሁሉም ሰው ህይወትሽን እንደ ፀሃይ ማብራት ይፈልጋል፡፡ እኔ ግን ጨረቃ መሆንን እመርጣለሁ፡፡ ፀሃይ የማይኖር ጊዜ ህይወትሽ ሲጨልም አበራልሻለሁ፡: ...

እንደምትወድህ እንዴት ታውቃለህ?

ብዙ ትንንሽ ነገሮችን አስባልህ ታደርጋለች  ማንኛውም ሰው (ወንድም ሆነ ሴት) ለማንም እንዲሁ አስቦ ብዙ  ውለታ አይውልም። አንዲት ሴት ሁል ጊዜ ትንንሽ መልካም ነገሮች የምታደርግህ ከሆነ እንደምታስብልህ ካንተ ጋር በፍቅር ወድቃ እንደሆነ መጠረጠር አለብህ። የሰራችልህን ዉለታ ሆነ የሰጠችህን ስጦታ አሳንሰህ አትመልከት። ዋናው ሀሳቡ ነው። አንተን ለማስደሰት ያን ያህል ከተጨነቀች በቃ ትወድሃለች ማለት ነው።  ታሳድድሃለች  የማማለል ጥበብ የሚያስተምረህ እንዴት ሴቶች እንዲያሳድዱህ ማድረግ ትችላለህ የሚለውን ነው። እንድታሳድድህ የማድረጊያ አንዱ መንገድ ደግሞ ካንተ ጋር በፍቅር እንድትወድቅ ማድረግ ነው። ከወደደችህ አንተን እንዳታሳድድህ የሚያደርጋት ነገር እምብዛም ነው። ሴቶች በተፈጥሮአቸው ለአላማ ፅኑዎች ናቸው። የምትፈልገው እንዳንተ አይነት ሰው እንደሆነ በቃልም በድርጊት ከነገረችህ እንደምትወድህ የምታውቅበት ግልፅ መንገድ ነው። ሴቶች ያልወደዱትን ወንድ በግልፅ አያሳድዱትም። ትነግርሃለች  ወንዶች ሳይወዱ እወድሻለሁ ሊሉ ይችላሉ። ነገር ግን ሴት ልጅ እወድሃለሁ ካለች እውነቷን እንደሆነ እወቅ። በቃ እመናት  ጊዜ እንድትሰጣት ትፈልጋለች  ጊዜህን በጣም በጣም ትፈልጋለች። ምናልባት ከስራ መልስ ቤትህ መጥታ እራት ልስራ ትላለች። ምናልባትም በምሳ እረፍቷ ቡና አብረሃት እንድትጠጣ ትጠራሃለች። ብቻ እንዴት ሆነ እንዴት ካንተ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ከፈለገች ትወድሃለች ማለት ነው።  ጓደኞቿ ስላንተ በጣም ያውቃሉ።  ጓደኞቿ መስማት ቢፈልጉም ባይፈልጉም ሁሌ ስላንተ ታወራላቸዋለች።  ታደንቅሃለች  በሙገሳ በ...

"ለልጅ ምክር ለአባት ማስታወሻ" ከሚል መፅሐፍ የተቀነጨበ

ሀሳብ አታብዛ ነገ ምን ይሆናል ብለህ አትጨነቅ። ምንም ሀሳብና ጭንቀት ብታበዛ የሚሆነው ነገር መሆኑ አይቀርም። ትልቅ ስልጣን ትፈልግ ይሆናል።ከሁሉ የሚበልጠው ግን ያለ ሀሳብና ጭንቀት መኖር ነው። ስለሆነው እንጂ ስለሚሆነው ነገር አትናገር።ሌሎችም ቢነግሩህ አትመናቸው። መልካም ነገር እያደረክ ወደ ፊት የሚሆነውን ጠብቅ። ሮጠህ ከማታመልጠው ነገር አትሽሽ። በልተህ ስትጠግብ ርሃብን ሀብታም ስትሆን ድህነትን ስትሾም ሽረትን አትርሳ።

ፍቅረኛሽ የምር እንደሚወድሽ እንዴት ታውቂያለሽ?

ፍቅረኛሽ የምር እንደሚወድሽ እንዴት ታውቂያለሽ? ወንድ ልጅ የህይወት አጋሩ ሊያደርጋት የሚፈልጋትን ሴት ሲያገኝ እርሷን ለመቅረብ፣ለማስደሰትና ከእርሷ ጋር ጊዜ ለማሳለፍ ማንኛውንም መስዋዕትነት ይከፍላል። የኔ እህት ከታች የተዘረዘሩትን ነገሮች የሚያደርግ ወንድ ካጋጠመሽ ጠበቅ አድርገሽ ያዢው። ከልቡ የሚያፈቅርሽ ወንድ የሚያሳያቸው ምልክቶች 1. #ከአንቺ_ጋር ለመሆን ቆራጥ ነው። ነገሮች ሲመቹ ብቻ ሳይሆን በአስቸጋሪ ጊዜ እንኳን ከአንቺ አይለይም። 2. ከችግሮች አይሸሽም። በግንኙነታችሁ ችግር ሲፈጠር እንዴት በእርጋታና በውይይት መፍታት እንዳለበት ያውቃል። ቂምን ወይም መጥፎ ስሜትን አፍኖ ማስቀመጥ አንድ ቀን እንደሚፈነዳ ያውቃል። ስለዚህ አለመግባባቶች ሲፈጠሩ ወዲያው ለማስተካከል ይጥራል። 3. ለትንንሽ ነገሮች እንኳን አትኩሮት ይሰጣል። አንቺ ትልቅ ቦታ የምትሰጪያቸውን ነገሮች ያውቃል። ለእርሱ ተራ መስሎ ቢታየውም እንኳን ያከብራል። አንቺ የምትወጂያቸው ምግቦች ቤት ውስጥ መኖራቸውን ያረጋግጣል። የምትወጂውን አይነት ፊልም ከአንቺ ጋር ካልሆነ አያይም።አንቺን ለማስደሰት ቤቱን በፅዳት ይይዛል። 4. ብልህና አስተዋይ ነው። ብልህነቱን እንዴት መጠቀም እንዳለበት ያውቃል። ምክር ይሰጥሻል፣ትክክለኛ ውሳኔዎችን ይወስናል። ልትተማመኚበት የምትችይው አይነት ሰው ነው። 5. ለራስሽ ፍቅር እንዲኖርሽ ይፈልጋል። 6. ስላንቺ ችግር እንደራሱ ችግር ይጨነቃል። ያንቺ ሀሳብ የእርሱም ሀሳብ ነው። በችግርሽ ጊዜ ከጎንሽ አይጠፋም። ግን ለራስሽ ጊዜ ስትፈልጊም ያውቃል። ብቸኝነት እንዲሰማሽ አይፈቅድም። በክንዶቹ እቅፍ አድርጎሽ ሁሉን ነገር ለማስተካከል ይጥራል። 7. በራሱም ሆነ ባንቺ ስህተት ስቆ ዝም ይላል። ማንም ሰው ፍፁም እንዳልሆነ ስለሚያውቅ አ...