ሁሌ በጥዋት ለፍቅር አጋርህ መልዕክት ብትልክላት የፍቅር ህይወትህን የበለጠ ያጣፍጠዋል፡፡ እንደምትወዳት እና የተለየች ሴት እንደሆነች እንዲሰማት ያደርጋል፡፡ ቀኗን ብሩህ ለማድረግ ከእነዚህ መል ዕክቶች የወደድከውን Copy Paste አድርገህ ላክላት፡፡ የኔ ፍቅር እንኳን አዲስ ቀን በህይወትሽ ተጨመረልሽ፡፡ አፈቅርሻለሁ እሺ፡፡ መልካም ቀን ይሁንልሽ፡፡ እየሰመጠ ያለ ሰው አየርን የሚወደውን ያህል እወድሻለሁ፡፡ ደስ የሚል ቀን ይሁንልሽ የኔ ውድ አንቺ ፊልም ብትሆኚ ብዙ ጊዜ ደጋግሜ አይሽ ነበር፡፡ ትክክለኛዋን ሴት ለማግኘት ብዙ ታግሻለሁ፡፡ በመጨረሻም ትዕግስቴ ፍሬ አፍርቶ አንቺን አግኝቻለሁ፡፡ ባየሁሽ ቁጥር እንደገና ፍቅር ይይዘኛል፡፡ አንቺ ለኔ ልዩ ሴት ነሽ፡፡ የአለማችን ቆንጅዬዋ ሴት እንዴት አደረች? በጧት ደስ የሚሉ ሀሳቦችን ማሰብ ቀኑን በደስታ ለማሳለፍ ወሳኝ ነው፡፡ ሁል ቀን ደስ ብሎኝ የምውለው አንቺን ስለማስብሽ ነው፡: ተደሰቺ ስለአንቺ ለሚጨነቅ ሰው መልዕክት ደርሶሻል፡፡ አንቺን ከማሰብ ጋር ፍቅር ይዞኛል ሁሉም ሰው ህይወትሽን እንደ ፀሃይ ማብራት ይፈልጋል፡፡ እኔ ግን ጨረቃ መሆንን እመርጣለሁ፡፡ ፀሃይ የማይኖር ጊዜ ህይወትሽ ሲጨልም አበራልሻለሁ፡: ...