ሁሌ በጥዋት ለፍቅር አጋርህ መልዕክት ብትልክላት
የፍቅር ህይወትህን የበለጠ ያጣፍጠዋል፡፡ እንደምትወዳት እና የተለየች ሴት እንደሆነች እንዲሰማት ያደርጋል፡፡ ቀኗን ብሩህ ለማድረግ
ከእነዚህ መልዕክቶች የወደድከውን Copy Paste አድርገህ ላክላት፡፡
- የኔ ፍቅር እንኳን አዲስ ቀን በህይወትሽ ተጨመረልሽ፡፡ አፈቅርሻለሁ እሺ፡፡ መልካም ቀን ይሁንልሽ፡፡
- እየሰመጠ ያለ ሰው አየርን የሚወደውን ያህል እወድሻለሁ፡፡ ደስ የሚል ቀን ይሁንልሽ የኔ ውድ
- አንቺ ፊልም ብትሆኚ ብዙ ጊዜ ደጋግሜ አይሽ ነበር፡፡
- ትክክለኛዋን ሴት ለማግኘት ብዙ ታግሻለሁ፡፡ በመጨረሻም ትዕግስቴ ፍሬ አፍርቶ አንቺን አግኝቻለሁ፡፡
- ባየሁሽ ቁጥር እንደገና ፍቅር ይይዘኛል፡፡ አንቺ ለኔ ልዩ ሴት ነሽ፡፡
- የአለማችን ቆንጅዬዋ ሴት እንዴት አደረች?
- በጧት ደስ የሚሉ ሀሳቦችን ማሰብ ቀኑን በደስታ ለማሳለፍ ወሳኝ ነው፡፡ ሁል ቀን ደስ ብሎኝ የምውለው አንቺን ስለማስብሽ ነው፡:
- ተደሰቺ ስለአንቺ ለሚጨነቅ ሰው መልዕክት ደርሶሻል፡፡
- አንቺን ከማሰብ ጋር ፍቅር ይዞኛል
- ሁሉም ሰው ህይወትሽን እንደ ፀሃይ ማብራት ይፈልጋል፡፡ እኔ ግን ጨረቃ መሆንን እመርጣለሁ፡፡ ፀሃይ የማይኖር ጊዜ ህይወትሽ ሲጨልም አበራልሻለሁ፡:
- የኔ ፍቅር ሁል ጊዜ ፊቴ ላይ ፈገግታ መዝራት ትችያለሽ፡፡
- በጣቶችሽ መሃል ያሉት ክፍተቶች ለምን እንደተፈጠሩ ታውቂያለሽ? የኔ ጣቶች እንዲገቡባቸው ነው፡፡
- በፈገግታሽ ብቻ በፍቅር የወደቀልሽ ሰው አለና ብትከፊ እንኳን ፊትሽን እንዳታኮሳትሪ፡፡
- በህይወቴ ትክክለኛ ነገር ያደረኩት ልቤን ለአንቺ የሰጠሁ ጊዜ ነው፡፡
- ለ 5 ሰከንድ ፈገግ ስላልሽ ፎቶሽ እንዴት እንደሚየምር አላየሽም? ሁሌም ፈገግ ብትይ ደግሞ ህይወትሽ ምን ሊመስል እንደሚችል መገመት አያቅትሽም፡፡ እናም የኔ ፍቅር ሁሌም ሳቅ በዪ፡፡
- በየጧቱ አንቺን ለማሰብ ሰከንድ ይበቃኛል፡፡አንቺን ሳስብ የሚሰማኝ ደስታ ግን ቀን ሙሉ ይቆያል፡፡
- እንዴት አደርሽ የኔ ውድ ? እንደ አበባ ፍክት ብለሽ ከእንቅለፍ እንደነቃሽ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
- በስልኬ ላይ ስምሽን ሳይ ያለኝ ደስታ ልዩ ነው፡፡
- ከዚህ በላይማ ልወዳት አልችልም እልና ሲነጋ ራሴን ብሶብኝ አገኘዋለሁ፡፡
- አንቺ ባለሽበት ቦታ እኮ ንዴትም ሀዘንም አይኖሩም ሁሉንም ነገር እንዴት ወደ ደስታ መቀየር እንደምትችይ ታውቂበታለሽ፡
- ፈገግታሽ ልቤን ያቀልጠዋል፡፡ደስታሽ ያስፈነድቀኛል፡፡ሳይሽ ልቤ ትርክክ ይላል፡፡
- የኔ ፍቅር ጧት ከእንቅልፌ ስነቃ ስለአንቺ አስባለሁ፡፡ ማታ ስተኛ ስለአንቺ አስባለሁ፡፡ በሁለቱ መካከል ስለአንቺ አስባለሁ፡፡
- ግን ሁሌ በሀሳቤ ስትመላለሺ እግርሽን አይደክምሽም?
- ልቤን ሰርቀሻል፡፡ በመሰረቁ ግን ደስተኛ ነኝ፡፡ ለኔ አልጠቀመኝም፡፡ በኔ ደረት ሆኖም የሚመታው ለአንቺ ነው፡፡
- መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ፡፡አንቺ ግን ከሀሉ ትበልጪያለሽ
- ሰዎች ፍቅር የሚይዘው አንዴ ነው ይላሉ፡፡ውሸታቸውን ነው፡፡እኔ ከአንቺ ጋር በየቀኑ እንደ አዲስ ነው የምይዘኝ፡፡
- እኔን የሚያስደስተኝ የአንቺ ደስታ ነው፡፡የደስታሽ ምክንያት እኔ ስሆን ደግሞ ደስታዬ እጥፍ ድርብ ይሆናል፡፡
- ስለፍቅር ሳስብ የማስበው አንቺን ነው፡፡ቆንጆ ነገሮችን ሳይ ትዝ የምትይኝ አንቺ ነሽ፡፡ የተደሰትኩ ቀን የሚሰማኝ አንቺ ከኔ ጋር እንዳለሽ ነው፡፡
- ከእንቅልፍ ስትነቂ የፈገግታሽ ምክንያት መሆን እፈልጋለሁ፡፡ ቀኑን ፍልቅልቅ ብለሽ እንድትውይ ምክንያት መሆን እፈልጋለሁ፡፡ ማታ ስትተኚ በደስተኛ ልብ እንድትተኚ ምክንያት መሆን እፈልጋለሁ፡፡ ከአጠገብሽ ስርቅ የምትናፍቂኝ ሰው መሆን እፈልጋለሁ፡፡
- ቀኑን በፈገግታ ጀምሪው ደስ ብሎሽ ትውያለሽ፡፡
Comments
Post a Comment