ማንኛውም ሰው (ወንድም ሆነ ሴት) ለማንም እንዲሁ አስቦ ብዙ ውለታ አይውልም። አንዲት ሴት ሁል ጊዜ ትንንሽ መልካም ነገሮች የምታደርግህ ከሆነ እንደምታስብልህ ካንተ ጋር በፍቅር ወድቃ እንደሆነ መጠረጠር አለብህ። የሰራችልህን ዉለታ ሆነ የሰጠችህን ስጦታ አሳንሰህ አትመልከት። ዋናው ሀሳቡ ነው። አንተን ለማስደሰት ያን ያህል ከተጨነቀች በቃ ትወድሃለች ማለት ነው።
ታሳድድሃለች
የማማለል ጥበብ የሚያስተምረህ እንዴት ሴቶች እንዲያሳድዱህ ማድረግ ትችላለህ የሚለውን ነው። እንድታሳድድህ የማድረጊያ አንዱ መንገድ ደግሞ ካንተ ጋር በፍቅር እንድትወድቅ ማድረግ ነው። ከወደደችህ አንተን እንዳታሳድድህ የሚያደርጋት ነገር እምብዛም ነው። ሴቶች በተፈጥሮአቸው ለአላማ ፅኑዎች ናቸው። የምትፈልገው እንዳንተ አይነት ሰው እንደሆነ በቃልም በድርጊት ከነገረችህ እንደምትወድህ የምታውቅበት ግልፅ መንገድ ነው። ሴቶች ያልወደዱትን ወንድ በግልፅ አያሳድዱትም።
ትነግርሃለች
ወንዶች ሳይወዱ እወድሻለሁ ሊሉ ይችላሉ። ነገር ግን ሴት ልጅ እወድሃለሁ ካለች እውነቷን እንደሆነ እወቅ። በቃ እመናት
ጊዜ እንድትሰጣት ትፈልጋለች
ጊዜህን በጣም በጣም ትፈልጋለች። ምናልባት ከስራ መልስ ቤትህ መጥታ እራት ልስራ ትላለች። ምናልባትም በምሳ እረፍቷ ቡና አብረሃት እንድትጠጣ ትጠራሃለች። ብቻ እንዴት ሆነ እንዴት ካንተ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ከፈለገች ትወድሃለች ማለት ነው።
ጓደኞቿ ስላንተ በጣም ያውቃሉ።
ጓደኞቿ መስማት ቢፈልጉም ባይፈልጉም ሁሌ ስላንተ ታወራላቸዋለች።
ታደንቅሃለች
በሙገሳ በጣም ካጥለቀለቀችህ እና ወዲያው ያንተ ቀንደኛ አድናቂ ከሆነች እንደምትወድህ ለመናገር እየሞከረች እንደሆነ አስተውል።
ስላንተ ትጨነቃለች
የምትወድህ ከሆነ ያንተ ደህንነትም ሆነ ጤንነት ያሳስባታል። ጉዳት ሲደርስብህ ወይም ችግር ውስጥ ስትገባ ታስብልሃለች።በቻለችው ሁሉ ከጎንህ ትቆማለች።
ለረጅም ጊዜ ካንተ ተለይታ መኖር አትፈልግም።
ለረጅም ጊዜ ሳታገኛት ስትቆይ የምትበሳጭ እና የሚሰማት ከሆነ ያ ብዙ ይናገራል። አንተ እለት ተእለት ህይወቷን ያላንተ ማሰብ እንደማትችል እና እንደምትናፍቃት ያሳያል። ይህ እንደምትወድህ ጠንካራ ማሳያ ነው።
ትቀናለች
ቅናት ከሰው ልጅ ስሜቶች አንዱ ሲሆን በጣም ትልቅ ቦታ የምትሰጠውን አንተን ላጣ ነው ብላ ስታስብ የሚሰማት ስሜት ነው።
ትንከባከብሃለች መስዋዕት ትሆንልሃለች
ከራሷ ይልቅ ላንተ ፍላጎት ቅድሚያ ትሰጣለች። ድካም ሆነ ርሃብ ሲሰማህ ታውቃለች። የምትጠላውንና የምትወደውን ታውቃለች። ግን ማወቅ ያለብህ ካንተም ተመሳሳይ ስሜት እንደምትጠብቅ ነው ።
Comments
Post a Comment