Skip to main content

መንጋጋ ቆልፍ(Tetanus)

መግቢያ


መንጋጋ ቆልፍ በባክቴሪያ መርዝ(toxin) የሚከሰት አደገኛ በሽታ ሲሆን የነርቭ ስርዓትን በመጉዳት ጡንቻዎች ከሚገባው በላይ እንዲኮማተሩ በማድረግ  የህመም ስሜት እንዲፈጠር ያደርጋል። አብዛኛውን ጊዜ በበሽታው የሚጠቁት የአንገት እና የመንጋጋ ጡንቻዎች ናቸው። ከዚህ የተነሳ አተነፋፈስ ላይ ችግር ስለሚያመጣ ለሞት ሊዳርግ ይችላል። 

የመንጋጋ ቆልፍ ክትባት ከተገኘለት በኋላ ባደጉ ሀገራት በእጅጉ የቀነሰ ሲሆን እንደ እኛ ሀገር በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ግን ተንሰራፍቶ ይገኛል። 

ለመንጋጋ ቆልፍ በሽታ ፈውስ የለም። የበሽታው ህክምና ትኩረት የሚሆነው የቴታነስ መርዝ ሰውነት ላይ ሊያስከትላቸው የሚችላቸውን ጉዳቶች በመቀነስ ላይ ነው። 

የበሽታው ምልክቶች 


የመንጋጋ ቆልፍ አምጪ ባክቴሪያ በሰውነታችን ላይ ባለ ቁስል ወደ ውስጥ ከገባ በኋላ ባሉት በጥቂት ቀናት ወይም ከበርካታ ሳምንታት በኋላ የበሽታው ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ።  በአማካይ ግን አስር ቀን ውስጥ የበሽታው ምልክቶች ይታያሉ። 
 በመንጋጋ ቆልፍ(Tetanus) የተጠቃ ህፃን

በብዛት የሚስተዋሉ የመንጋጋ ቆልፍ ምልክቶች 


  •  የመንጋጋ ጡንቻዎች መገታተር 
  • የአንገት ጡንቻዎች መገታተር 
  •  ለመዋጥ መቸገር 
  •  የሆድ ጡንቻዎች መገታተር 
  •  የህመም ስሜት ያለው የጡንቻዎች መወጣጠር ( በብርሃን፣በከፍተኛ ድምፅ፣በንክኪ) ሊቀሰቀስ ይችላል። 

ሌሎች ሊኖሩ የሚችሉ ምልክቶች 


  • ትኩሳት 
  • ላብ 
  • የደም ግፊት መጨመር
  • የልብ ምት መጨመር 

መንስኤ 


የመንጋጋ ቆልፍ(tetanus) በሽታን የሚያመጣው ክሎስትሪድየም ቴታኒ የሚባል ባክቴሪያ የሚሰራው መርዝ ነው።  ክሎስትሪድየም ቴታኒ በአፈር በአቧራ እና በእንስሳት አይነ-ምድር ላይ ይገኛል። ባክቴሪያው በሰውነታችን ባለ ቁስል ወደ ውስጥ ከገባ በኋላ ቴታኖስፓስሚን የሚባል አደገኛ መርዝ ያመርታል። ይህ መርዝ ጡንቻዎቻችንን የሚያዙ ነርቮችን ስራ ያስተጓጉላል። በዚህ ምክኒያት የበሽታው መለያ የሆነው የጡንቻዎች መገታተር ይከሰታል። 

ከሞላ ጎደል ሁሉም የበሽታው ተጠቂዎች የመንጋጋ ቆልፍ ክትባት ጭራሽ ያልወሰዱ ወይም ከወሰዱ አስር አመት ያለፋቸው ሰዎች ናቸው። የመንጋጋ ቆልፍ ከሰው ወደ ሰው አይተላለፍም። 

አጋላጭ ሁኔታዎች(Risk factors )


ከታች የተዘረዘሩት ነገሮች በመንጋጋ ቆልፍ የመያዝ እድልን ይጨምራሉ።


  • የመንጋጋ ቆልፍ ክትባት አለመከተብ 
  • ሰውነት ላይ ያለ ቁስል
  • በሰውነታችን ያለ ባዕድ ነገር ( ሰው ሰራሽ ጥፍር ወይም ስንጥር)

መንጋጋ ቆልፍ ከእነዚህ ሊነሳ ይችላል።


  • ሰውነት በመወጋት የተከሰተ ቁስል( በስንጥር፣ሰውነት በመበሳት፣ንቅሳት፣ በመርፌ የሚወሰዱ እፆች በመጠቀም)
  • የጥይት ቁስል
  • ክፍት የአጥንት ስብራት 
  • ቃጠሎ 
  • የቀዶ ህክምና ቁስል 
  • የእንስሳት ወይም የነፍሳት ንክሻ 
  • ያመረቀዘ የእግር ቁስል 
  • የጥርስ እንፌክሽን 
  • ያልተከተቡ እናቶች በሚወልዷቸው ጨቅላ ህፃናት እትብት ላይ የሚፈጠር እንፌክሽን 
  • በሀገራችን ደግሞ እትብትን ንፅህና በጎደለው ነገር መቁረጥ ( በዛገ ምላጭ) ወይም እትብት ላይ የተለያዩ ነገሮች በመጨመር ( አፈር፣ ቅቤ ወዘተ)

ጉዳቶች ( Complications)


አንድ ጊዜ የቴታነስ መርዝ ከነርቭ ጋር ከተጣበቀ ማላቀቅ አይቻልም። ከመንጋጋ ቆልፍ በሽታ ሙሉ በሙሉ ለማገገም አዳዲስ ነርቮች ከነርቭ መጨረሻ ላይ ማደግ አለባቸው። ያ ደግሞ ብዙ ወራትን ሊፈጅ ይችላል። 

የመንጋጋ ቆልፍ(tetanus) በሽታ ጉዳቶች እነዚህን ያካትታሉ።  


  • የአጥንት ስብራት፦ ከባድ የጡንቻ መወጣጠር ስለሚኖር የአከርካሪና እና ሌሎች አጥንቶች ስብራት ሊፈጠር ይችላል። 
  • የሳንባ ደም ሰር መዘጋት 
  • ሞት፦ አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰተው ለመተንፈስ የምንጠቀማቸው ጡንቻዎች ተገትረው ስለሚቀሩ በአተነፋፈስ ችግር ነው። 

መከላከያው 


በክትባት በቀላሉ ልንከላከለው የምንችለው በሽታ ነው። 

ምርመራው 


በሽታውን ለመለየት የሚጠቅም የላብራቶሪ ምርመራ የለም። ሀኪሞች በሽታውን የሚለዩት በምልክቶቹ ነው። 

ህክምናው 


በሽታውን የሚፈውስ መድሃኒት የለም። ህክምናው ቁስል ካለ ቁስሉን ማከም፣ምልክቶቹን መቀነስ እና የድጋፍ እርዳታዎችን ያካትታል።

የቁስል ህክምና 


ቁስልን በሚገባ ማፅዳት የበሽታው አምጪ ባክቴሪያ እንዳይራባ ያደርጋል። ቁስል ላይ ያለ ቆሻሻ የሞቱ ህዋሳት ወይም ባዕድ ነገሮች ካሉ ማስወገድ 

መድሃኒቶች 


የመርዝ ማርከሻ(Antitoxon) ይሄ ከነርቭ ጋር ያልተያየዙ መርዞችን ይይዛቸዋል። 
አንቲባዮቲክ፦ የቴታነስ ባክቴሪያን ይገድላል።
ክትባት፦ሁሉም የበሽታው ተጠቂ ክትባቱን መውሰድ አለበት። 
ሴዳቲቭስ፦የጡንቻ መወጣጠርን ይቀንሳሉ። 











Comments

Post a Comment

Popular posts from this blog

በጧት የሚላኩ የፍቅር መልዕክቶች

  ሁሌ በጥዋት ለፍቅር አጋርህ መልዕክት ብትልክላት የፍቅር ህይወትህን የበለጠ ያጣፍጠዋል፡፡ እንደምትወዳት እና የተለየች ሴት እንደሆነች እንዲሰማት ያደርጋል፡፡ ቀኗን ብሩህ ለማድረግ ከእነዚህ መል ዕክቶች   የወደድከውን Copy Paste አድርገህ ላክላት፡፡        የኔ   ፍቅር እንኳን አዲስ ቀን በህይወትሽ ተጨመረልሽ፡፡ አፈቅርሻለሁ እሺ፡፡ መልካም ቀን ይሁንልሽ፡፡        እየሰመጠ ያለ ሰው አየርን የሚወደውን ያህል እወድሻለሁ፡፡ ደስ የሚል ቀን ይሁንልሽ የኔ ውድ          አንቺ ፊልም ብትሆኚ ብዙ ጊዜ ደጋግሜ አይሽ ነበር፡፡        ትክክለኛዋን ሴት ለማግኘት ብዙ ታግሻለሁ፡፡ በመጨረሻም ትዕግስቴ ፍሬ አፍርቶ አንቺን አግኝቻለሁ፡፡       ባየሁሽ ቁጥር እንደገና ፍቅር ይይዘኛል፡፡ አንቺ ለኔ ልዩ ሴት ነሽ፡፡        የአለማችን ቆንጅዬዋ ሴት እንዴት አደረች?         በጧት ደስ የሚሉ ሀሳቦችን ማሰብ ቀኑን በደስታ ለማሳለፍ ወሳኝ ነው፡፡ ሁል ቀን ደስ ብሎኝ የምውለው አንቺን ስለማስብሽ ነው፡:              ተደሰቺ ስለአንቺ ለሚጨነቅ ሰው መልዕክት ደርሶሻል፡፡        አንቺን ከማሰብ ጋር ፍቅር ይዞኛል       ሁሉም ሰው ህይወትሽን እንደ ፀሃይ ማብራት ይፈልጋል፡፡ እኔ ግን ጨረቃ መሆንን እመርጣለሁ፡፡ ፀሃይ የማይኖር ጊዜ ህይወትሽ ሲጨልም አበራልሻለሁ፡: ...

እንደምትወድህ እንዴት ታውቃለህ?

ብዙ ትንንሽ ነገሮችን አስባልህ ታደርጋለች  ማንኛውም ሰው (ወንድም ሆነ ሴት) ለማንም እንዲሁ አስቦ ብዙ  ውለታ አይውልም። አንዲት ሴት ሁል ጊዜ ትንንሽ መልካም ነገሮች የምታደርግህ ከሆነ እንደምታስብልህ ካንተ ጋር በፍቅር ወድቃ እንደሆነ መጠረጠር አለብህ። የሰራችልህን ዉለታ ሆነ የሰጠችህን ስጦታ አሳንሰህ አትመልከት። ዋናው ሀሳቡ ነው። አንተን ለማስደሰት ያን ያህል ከተጨነቀች በቃ ትወድሃለች ማለት ነው።  ታሳድድሃለች  የማማለል ጥበብ የሚያስተምረህ እንዴት ሴቶች እንዲያሳድዱህ ማድረግ ትችላለህ የሚለውን ነው። እንድታሳድድህ የማድረጊያ አንዱ መንገድ ደግሞ ካንተ ጋር በፍቅር እንድትወድቅ ማድረግ ነው። ከወደደችህ አንተን እንዳታሳድድህ የሚያደርጋት ነገር እምብዛም ነው። ሴቶች በተፈጥሮአቸው ለአላማ ፅኑዎች ናቸው። የምትፈልገው እንዳንተ አይነት ሰው እንደሆነ በቃልም በድርጊት ከነገረችህ እንደምትወድህ የምታውቅበት ግልፅ መንገድ ነው። ሴቶች ያልወደዱትን ወንድ በግልፅ አያሳድዱትም። ትነግርሃለች  ወንዶች ሳይወዱ እወድሻለሁ ሊሉ ይችላሉ። ነገር ግን ሴት ልጅ እወድሃለሁ ካለች እውነቷን እንደሆነ እወቅ። በቃ እመናት  ጊዜ እንድትሰጣት ትፈልጋለች  ጊዜህን በጣም በጣም ትፈልጋለች። ምናልባት ከስራ መልስ ቤትህ መጥታ እራት ልስራ ትላለች። ምናልባትም በምሳ እረፍቷ ቡና አብረሃት እንድትጠጣ ትጠራሃለች። ብቻ እንዴት ሆነ እንዴት ካንተ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ከፈለገች ትወድሃለች ማለት ነው።  ጓደኞቿ ስላንተ በጣም ያውቃሉ።  ጓደኞቿ መስማት ቢፈልጉም ባይፈልጉም ሁሌ ስላንተ ታወራላቸዋለች።  ታደንቅሃለች  በሙገሳ በ...