የተወሰነ ጭንቀት ወይም መረበሽ የህይወት አንድ አካል ነው። ነገር ግን የጭንቀት ህመም ያለባቸው ሰዎች በእለት ተእለት ኑሮዋቸው ሀይለኛ እና የማያቋርጥ የመረበሽ እና ፍርሃት ስሜት ሁል ጊዜ ይስተዋልባቸዋል። የጭንቀት ታማሚዎች አብዛኛውን ጊዜ በተደጋጋሚ ድንገት የሚከሰት ሀይለኛ የፍርሃት፣የመጨነቅ እና የመሸበር ስሜት የሚገጥማቸው ሲሆን ይህ ስሜት በደቂቃዎች ውስጥ ጣራ ይነካል። Panic attack በመባልም ይታወቃል። እነዚህ የጭንቀት እና ሽብር ምልክቶች የእለት-ተእለት ስራችንን በአግባቡ እንዳናከናውን የሚያደርጉ፣ለመቆጣጠር የሚያስቸግሩ፣ በቂ ምክኒያት የሌላቸው እና ለብዙ ጊዜ የሚቀጥሉ ናቸው። ምልክቶቹ በልጅነት ወይም በጉርምስና ወቅት የሚጀምሩ ሲሆን እስከ አዋቂነት የሚቀጥሉ ናቸው። የጭንቀት ህመሞች በርካታ አይነት ሲሆኑ የሚከተሉት ይገኙባቸዋል። ጠቅላላ የጭንቀት ህመም(Generalized Anxiety disorder),የማህበረሰብ ፍርሃት(Social anxiety disorder <Social phobia>), የተወሰነ ምክኒያት አልባ ፍርሃት ( Specific phobia) የመለያየት ጭንቀት( Separation anxiety disorder ). በአንድ ሰው ላይ ከአንድ አይነት በላይ የጭንቀት ህመም ሊከሰት ይችላል። ጭንቀት አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ህክምና የሚያስፈልገው ሌላ የውስጥ ደዌ ምልክት ሊሆን ይችላል። የትኛውም አይነት የጭንቀት ህመም ቢኖርቦት ህክምና ማድረጉ ይረዳዎታል። ምልክቶች በብዛት የሚስተዋሉ የጭንቀት ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው። ውጥረት የመቅበጥበጥ የመደንገጥ ስሜት "የሆነ ከባድ ዱብ እዳ ሊመጣብኝ ነው።"ብሎ ማሰብ የልብ ምት መጨመ...