Skip to main content

የጭንቀት ህመሞች( Anxiety disorders )



የተወሰነ ጭንቀት ወይም መረበሽ የህይወት አንድ አካል ነው። ነገር ግን የጭንቀት ህመም ያለባቸው ሰዎች በእለት ተእለት ኑሮዋቸው ሀይለኛ እና የማያቋርጥ የመረበሽ እና ፍርሃት ስሜት ሁል ጊዜ ይስተዋልባቸዋል። የጭንቀት ታማሚዎች አብዛኛውን ጊዜ በተደጋጋሚ ድንገት የሚከሰት ሀይለኛ የፍርሃት፣የመጨነቅ እና የመሸበር ስሜት  የሚገጥማቸው ሲሆን ይህ ስሜት በደቂቃዎች ውስጥ ጣራ ይነካል። Panic attack በመባልም ይታወቃል።

እነዚህ የጭንቀት እና ሽብር ምልክቶች የእለት-ተእለት ስራችንን  በአግባቡ እንዳናከናውን የሚያደርጉ፣ለመቆጣጠር የሚያስቸግሩ፣ በቂ ምክኒያት የሌላቸው እና ለብዙ ጊዜ የሚቀጥሉ ናቸው። ምልክቶቹ በልጅነት ወይም በጉርምስና ወቅት የሚጀምሩ ሲሆን እስከ አዋቂነት የሚቀጥሉ ናቸው።

የጭንቀት ህመሞች በርካታ አይነት ሲሆኑ የሚከተሉት ይገኙባቸዋል። 


ጠቅላላ የጭንቀት ህመም(Generalized Anxiety disorder),የማህበረሰብ ፍርሃት(Social anxiety disorder <Social phobia>), የተወሰነ ምክኒያት አልባ ፍርሃት ( Specific phobia) የመለያየት ጭንቀት( Separation anxiety disorder ). በአንድ ሰው ላይ ከአንድ አይነት በላይ የጭንቀት ህመም ሊከሰት ይችላል። ጭንቀት  አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ህክምና የሚያስፈልገው ሌላ የውስጥ ደዌ ምልክት ሊሆን ይችላል።

የትኛውም አይነት የጭንቀት ህመም ቢኖርቦት ህክምና ማድረጉ ይረዳዎታል።

ምልክቶች 


በብዛት የሚስተዋሉ የጭንቀት ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው።

  • ውጥረት የመቅበጥበጥ የመደንገጥ ስሜት 
  • "የሆነ ከባድ ዱብ እዳ ሊመጣብኝ ነው።"ብሎ ማሰብ 
  • የልብ ምት መጨመር 
  • ቶሎ ቶሎ መተንፈስ 
  • ማላብ 
  • መንቀጥቀጥ 
  • የድካም ስሜት( ሳይሰሩ) 
  • ከሚያስጨንቀው ነገር ውጭ ሌላ ነገር አለማሰብ ወይም ትኩረት ማጣት 
  • የእንቅልፍ ችግር 
  • የምግብ አለመፈጨት ወይም የጨጓራ ህመም 
  • የሚያስጨንቁትን ነገሮች ለማስወገድ የሚኖር ከፍተኛ ፍላጎት 

ሀኪም ማማከር ያለብህ መቼ ነው?



  • ከመጠን በላይ እየተጨነቅክ ከሆነ እና ያ በስራህም ሆነ በማህበራዊ ህይወትህ ችግር ከፈጠረ 
  • ፍርሃትህ ወይም ጭንቀትህ አንተን እየረበሸህ ከሆነና ልትቀጣጠረው ካልቻልክ 
  • ድብርት የሚሰማህ ከሆነ ወይም  ደባል ሱስ ካለብህ ሌላ የአዕምሮ ህመም ካለብህ 
  • ጭንቀቱ የተከሰተብህ ከሌላ አካላዊ ህመም የተነሳ እንደሆነ ከተሰማህ 
  • ራስህን አጥፋ የሚል ሀሳብ ከመጣብህ ወይም ተግባር ውስጥ ከገባህ አፋጣኝ ህክምና ማግኘት አለብህ።


አስተውል። ጭንቀቶች በጊዜ ሂደት ላይጠፉ፤ህክምና ካላገኘህ እንዲያውም ሊባባሱ ይችላሉ። ሀኪም በጊዜ ማማከሩ የተሻለ ነው። በቆየ ቁጥር ህክምናው አስቸጋሪ ይሆናል።

መንስኤ 


የጭንቀት ህመሞች መንስኤ በትክክል አይታወቅም። በህይወት የሚገጥሙ አስቸጋሪ ነገሮች ለበሽታው ብልባሌ ( Prone) በሆኑ ሰዎች ሲከሰቱ። በቤተሰብ የመወራረስ ነገርም ሊኖረው ይችላል።

አንዳንዴ ጭንቀት የመድሃኒቶች የጎንዮሽ ጠንቅ( Side  effect) ሊሆን ይችላል።

አጋላጭ ሁኔታዎች ( Risk factors) 


እነዚህ ከታች የተዘረዘሩት ነገሮች በጭንቀት ህመም የመጠቃት እድላችንን ይጨምራሉ።

አሰቃቂ አደጋ


ስቃይ የደረሰባቸው ወይም አሰቃቂ አደጋ በልጅነታቸው ያዩ ሰዎች ለጭንቀት ህመም የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው።

በህመም ምክኒያት የሚከሰት ውጥረት፦ ከባድ ህመም ያለበት ሰው ስለ ህመሙ ስለህክምናው እና ስለወደፊት ህይወቱ ሊጨነቅ ይችላል።

የውጥረቶች መደራረብ


 ትልቅ ውጥረት የሚፈጥር  ክስተት ወይም ትናንሽ አስጨናቂ ክስተቶች ተደማምረው የጭንቀት ህመምን ሊቀሰቅሱ ይችላሉ። ለምሳሌ የቤተሰብ ሞት፣የስራ ጫና እና የገንዘብ ችግር።

ጉዳቶች( Complications)



  • ድብርት
  • የአደንዛዥ ዕፅ ሱስ 
  • የእንቅልፍ ማጣት 
  • ራስ ምታት እና የማይቆም ህመም 
  • የስርዓተ-ልመት ችግሮች 
  • ከማህበረሰብ ተለይቶ መኖር 
  • በስራም ሆነ በትምህርት የውጤት ማሽቆልቆል። 
  • ራስን ማጥፋት 


እንዴት መከላከል ይቻላል?


በጊዜ እርዳታ በማግኘት 

በንቃት መኖር 

የሚያስደስትህን እና ስለራስህ ጥሩ ስሜት እንዲሰማህ የሚያደርጉ ነገሮችን አድርግ። ከሰዎች ጋር ያለህን ማህበራዊ ግንኙነት አጠናክር።

አልኮል አትጠጣ ሌሎች አደንዛዥ ዕፆችንም አትጠቀም። 


በሱስ ከተጠመድክ ለመውጣትም ከከበደህ ሀኪም አማክር። 

Comments

Popular posts from this blog

በጧት የሚላኩ የፍቅር መልዕክቶች

  ሁሌ በጥዋት ለፍቅር አጋርህ መልዕክት ብትልክላት የፍቅር ህይወትህን የበለጠ ያጣፍጠዋል፡፡ እንደምትወዳት እና የተለየች ሴት እንደሆነች እንዲሰማት ያደርጋል፡፡ ቀኗን ብሩህ ለማድረግ ከእነዚህ መል ዕክቶች   የወደድከውን Copy Paste አድርገህ ላክላት፡፡        የኔ   ፍቅር እንኳን አዲስ ቀን በህይወትሽ ተጨመረልሽ፡፡ አፈቅርሻለሁ እሺ፡፡ መልካም ቀን ይሁንልሽ፡፡        እየሰመጠ ያለ ሰው አየርን የሚወደውን ያህል እወድሻለሁ፡፡ ደስ የሚል ቀን ይሁንልሽ የኔ ውድ          አንቺ ፊልም ብትሆኚ ብዙ ጊዜ ደጋግሜ አይሽ ነበር፡፡        ትክክለኛዋን ሴት ለማግኘት ብዙ ታግሻለሁ፡፡ በመጨረሻም ትዕግስቴ ፍሬ አፍርቶ አንቺን አግኝቻለሁ፡፡       ባየሁሽ ቁጥር እንደገና ፍቅር ይይዘኛል፡፡ አንቺ ለኔ ልዩ ሴት ነሽ፡፡        የአለማችን ቆንጅዬዋ ሴት እንዴት አደረች?         በጧት ደስ የሚሉ ሀሳቦችን ማሰብ ቀኑን በደስታ ለማሳለፍ ወሳኝ ነው፡፡ ሁል ቀን ደስ ብሎኝ የምውለው አንቺን ስለማስብሽ ነው፡:              ተደሰቺ ስለአንቺ ለሚጨነቅ ሰው መልዕክት ደርሶሻል፡፡        አንቺን ከማሰብ ጋር ፍቅር ይዞኛል       ሁሉም ሰው ህይወትሽን እንደ ፀሃይ ማብራት ይፈልጋል፡፡ እኔ ግን ጨረቃ መሆንን እመርጣለሁ፡፡ ፀሃይ የማይኖር ጊዜ ህይወትሽ ሲጨልም አበራልሻለሁ፡: ...

እንደምትወድህ እንዴት ታውቃለህ?

ብዙ ትንንሽ ነገሮችን አስባልህ ታደርጋለች  ማንኛውም ሰው (ወንድም ሆነ ሴት) ለማንም እንዲሁ አስቦ ብዙ  ውለታ አይውልም። አንዲት ሴት ሁል ጊዜ ትንንሽ መልካም ነገሮች የምታደርግህ ከሆነ እንደምታስብልህ ካንተ ጋር በፍቅር ወድቃ እንደሆነ መጠረጠር አለብህ። የሰራችልህን ዉለታ ሆነ የሰጠችህን ስጦታ አሳንሰህ አትመልከት። ዋናው ሀሳቡ ነው። አንተን ለማስደሰት ያን ያህል ከተጨነቀች በቃ ትወድሃለች ማለት ነው።  ታሳድድሃለች  የማማለል ጥበብ የሚያስተምረህ እንዴት ሴቶች እንዲያሳድዱህ ማድረግ ትችላለህ የሚለውን ነው። እንድታሳድድህ የማድረጊያ አንዱ መንገድ ደግሞ ካንተ ጋር በፍቅር እንድትወድቅ ማድረግ ነው። ከወደደችህ አንተን እንዳታሳድድህ የሚያደርጋት ነገር እምብዛም ነው። ሴቶች በተፈጥሮአቸው ለአላማ ፅኑዎች ናቸው። የምትፈልገው እንዳንተ አይነት ሰው እንደሆነ በቃልም በድርጊት ከነገረችህ እንደምትወድህ የምታውቅበት ግልፅ መንገድ ነው። ሴቶች ያልወደዱትን ወንድ በግልፅ አያሳድዱትም። ትነግርሃለች  ወንዶች ሳይወዱ እወድሻለሁ ሊሉ ይችላሉ። ነገር ግን ሴት ልጅ እወድሃለሁ ካለች እውነቷን እንደሆነ እወቅ። በቃ እመናት  ጊዜ እንድትሰጣት ትፈልጋለች  ጊዜህን በጣም በጣም ትፈልጋለች። ምናልባት ከስራ መልስ ቤትህ መጥታ እራት ልስራ ትላለች። ምናልባትም በምሳ እረፍቷ ቡና አብረሃት እንድትጠጣ ትጠራሃለች። ብቻ እንዴት ሆነ እንዴት ካንተ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ከፈለገች ትወድሃለች ማለት ነው።  ጓደኞቿ ስላንተ በጣም ያውቃሉ።  ጓደኞቿ መስማት ቢፈልጉም ባይፈልጉም ሁሌ ስላንተ ታወራላቸዋለች።  ታደንቅሃለች  በሙገሳ በ...

መንጋጋ ቆልፍ(Tetanus)

መግቢያ መንጋጋ ቆልፍ በባክቴሪያ መርዝ(toxin) የሚከሰት አደገኛ በሽታ ሲሆን የነርቭ ስርዓትን በመጉዳት ጡንቻዎች ከሚገባው በላይ እንዲኮማተሩ በማድረግ  የህመም ስሜት እንዲፈጠር ያደርጋል። አብዛኛውን ጊዜ በበሽታው የሚጠቁት የአንገት እና የመንጋጋ ጡንቻዎች ናቸው። ከዚህ የተነሳ አተነፋፈስ ላይ ችግር ስለሚያመጣ ለሞት ሊዳርግ ይችላል።  የመንጋጋ ቆልፍ ክትባት ከተገኘለት በኋላ ባደጉ ሀገራት በእጅጉ የቀነሰ ሲሆን እንደ እኛ ሀገር በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ግን ተንሰራፍቶ ይገኛል።  ለመንጋጋ ቆልፍ በሽታ ፈውስ የለም። የበሽታው ህክምና ትኩረት የሚሆነው የቴታነስ መርዝ ሰውነት ላይ ሊያስከትላቸው የሚችላቸውን ጉዳቶች በመቀነስ ላይ ነው።  የበሽታው ምልክቶች  የመንጋጋ ቆልፍ አምጪ ባክቴሪያ በሰውነታችን ላይ ባለ ቁስል ወደ ውስጥ ከገባ በኋላ ባሉት በጥቂት ቀናት ወይም ከበርካታ ሳምንታት በኋላ የበሽታው ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ።  በአማካይ ግን አስር ቀን ውስጥ የበሽታው ምልክቶች ይታያሉ።   በመንጋጋ ቆልፍ(Tetanus) የተጠቃ ህፃን በብዛት የሚስተዋሉ የመንጋጋ ቆልፍ ምልክቶች   የመንጋጋ ጡንቻዎች መገታተር  የአንገት ጡንቻዎች መገታተር   ለመዋጥ መቸገር   የሆድ ጡንቻዎች መገታተር   የህመም ስሜት ያለው የጡንቻዎች መወጣጠር ( በብርሃን፣በከፍተኛ ድምፅ፣በንክኪ) ሊቀሰቀስ ይችላል።  ሌሎች ሊኖሩ የሚችሉ ምልክቶች  ትኩሳት  ላብ  የደም ግፊት መጨመር የልብ ምት መጨመር  መንስኤ  ...